በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ ምሽት ተጠባቂ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

0
131

ባሕር ዳር: የካቲት 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ ምሽት አራት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

ከእነዚህ ጨዋታዎች መካከል ሴልቲክ ከባየርን ሙኒክ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። ጨዋታው ምሽት 5:00 ይካሄዳል።

ሁለቱ ቡድኖች እስካሁን አራት ጊዜ ተገናኝገዋል። ባየርን ሙኒክ በግንኙነታቸው የበላይነት አለው። በሦስቱ ሲያሸንፍ አንድ ጊዜ አቻ ወጥተዋል። የዛሬውን ጨዋታስ ማን ያሸንፋል የሚለው በጉጉት ይጠበቃል።

የዛሬው ጨዋታ በ1888 እንደተገነባ በሚነገርለት እና 60ሺህ 411 ተመልካች የማስተናገድ አቅም ባለው ሴልቲክ ፓርክ ስታዲየም ይደረጋል።

ሌላው ተጠባቂ ጨዋታ ፌይኖርድ ከኤሲ ሚላን የሚያደርጉት ጨዋታ ነው። ሁለቱ ቡድኖች ሁለት ጊዜ እርስ በእርስ የመገናኘት ዕድል ነበራቸው። በግንኙነታቸው አንዳንድ ጊዜ ተሸናንፈዋል። ጨዋታውም 5 ሰዓት ይካሄዳል።

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሌሎች ጨዋታዎችም ሲካሄዱ ክለብ ብሩጅ ከአታላንታ ምሽት 2:45 የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። ሞናኮ ከቤንፊካ ምሽት 5:00 ይጫወታሉ።

በአውሮፓ ሻምፒዎንስ ጥሎ ማለፍ ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች በተጠባቂው ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ማንቸስተር ሲቲን 3ለ2 አሸንፏል።ፒኤስጂ ብሬስትን 3ለ0፤ ጁቬንቱስ ፒኤስቪን 2ለ1፤ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ስፖርቲንግ ሊዝበንን 3ለ0 በኾነ ውጤት ማሸነፋቸው ይታወሳል።

በምሥጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here