ባሕር ዳር: ጥር 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት ጨዋታ ሊቨርፑል ከሜዳው ውጭ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በቪታሊቲ ስታዲየም ከበርንማውዝ ጋር ይጫወታል።
ሊቨርፑል እስካሁን 22 ጨዋታዎችን በማድረግ በ16 ጨዋታዎች አሸንፏል።በአምስቱ አቻ ተለያይቶ የተሸነፈው በአንድ ጨዋታ ብቻ ነው። በ53 ነጥብም ሊጉን በመምራት ላይ ነው።
በርንማውዝ በበኩሉ ከ23 ጨዋታዎች በ11 አሸንፎ፣ በሰባቱ አቻ ተለያይቶ እና በአምስቱ ተረትቶ በ40 ነጥብ በሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ሊቨርፑል መሪነቱን አጠናክሮ ለመቀጠል፤ በርንማውዝ ደግሞ ትልልቅ ቡድኖችን እያሸነፈ በመምጣቱ እና ወደ መሪዎች ለመጠጋት ብርቱ ጨዋታ ያደርጋሉ ተብሎ ተጠብቋል።
ቀን 9፡30 ላይም ኖቲንግሃም ፎረስት ከብራይተን ይጫወታሉ። ምሽት 12 ሰዓት ላይ ደግሞ ኤቨርተን ከሌስተር ሲቲ፣ ኢፕስዊች ታውን ከሳውዝ ሀምተን፣ ኒውካስትል ዩናይትድ ከፉልሀም ይጫወታሉ።
ምሽት 2:30 ወልቭስ በሜዳው አስቶንቪላን ያስተናግዳል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



