በ17ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

0
163

ባሕር ዳር: ጥር 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ ከሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች መካከል ባሕር ዳር ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች በተመሳይ የወጥነት ጥያቄ የሚነሳባቸው ሰለመኾኑ በቅርብ ካደረጓቸው ጨዋታዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡

ባሕር ዳር ከተማ አሁን በ23 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ አምስተኛ ላይ ተቀምጧል። የዛሬውን ጨዋታ ደረጃውን ለማሻሻል እና የቡድኑን የተፎካከሪነት መንፈስ ለመመለስ ይጫወታል ተብሎ ነው የሚጠበቀው፡፡

በተመሳሳይ በደረጃ ሰንጠረዡ በ19 ነጥብ 10ኛ ላይ ያለው ኢትዮጵያ ቡና ካለበት የአቋም መዋዥቅ ለመውጣት የዛሬውን ውጤት ለማገኘት ወደ ሜዳ ይገባል።

ሁለቱ ቡድኖች በቅርብ ሦስት ጨዋታዎች ተመሳሳይ አቋም አሳይተዋል። ከሦስት ጨዋታዎች አንዱን ሲያሸንፉ አንዱን ተሸንፈው አንድ አቻ ተለያያተዋል፡፡

እርስ በርስም እስካሁን 11 ጊዜ የመገናኘት ዕድል ገጥሟቸው ነበር፡፡ ማሸነፍ ላይ ባሕር ዳር ከተማ የተሻለ ሲኾን አምስት ጊዜ ሲረታ አንድ ጊዜ ተሸንፎ አምስት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥቷል፡፡

ጨዋታው ምሽት 12 ሰዓት ላይ ይካሄዳል፡፡

በሌላ የዛሬ ጨዋታ ወላይታ ድቻ እና ቅዱስ ጊወርጊስ ይገናኛሉ፡፡ ጨዋታውም ቀን 9 ሰዓት ላይ ይካሄዳል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here