ባሕር ዳር: ጥር 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በ2024/25 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ 36 ክለቦች በዙር እየተሳተፉበት ይገኛሉ፡፡ ዛሬ የሰባተኛ ዙር ጨዋታዎች በተለያዩ ከተሞች ቀጥለው ይካሄዳሉ፡፡
ምሽት2፡45 ላይ ያደረጋቸውን ስድስት ጨዋታዎች በሙሉ ተሸንፎ 35ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አር.ቢ ሌፕዚግ 10 ነጥብ በመያዝ 19ኛ ላይ ከተቀመጠው ስፖርቲንግ ሊዝበን ጋር ይጫዎታሉ።
በስድስት ጨዋታዎች አራት ነጥብ በመያዝ 28ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሻካታር ዶኔስክ በ13 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ካለው ብሬስት ጋር ይገናኛሉ፡፡
ምሽት 5 ስዓት ላይ አርሰናል ከዳይናሞ ዛግሬብ የሚያደርጉትም ሌላው ተጠባቂ ጨዋታ ነው፡፡
አርሰናል ከስድስት ጨዋታዎች በአራቱ አሸንፎ፤ በአንዱ አቻ ተለያይቶ እና በአንዱ ደግሞ ተሸንፎ በ13 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
ተጋጣሚው ዳይናሞ ዛግሬብ በበኩሉ ከስድስት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው ሁለቱን ብቻ ነው፡፡ በስምንት ነጥብም 25ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ አርሰናል በጨዋታው ካሸነፈ ደረጃውን ወደ ሦስተኛ ከፍ ማድረግ የሚችልበት ዕድል አለ።
ሌሎች ጨዋታዎችም ምሽት 5 ስዓት ላይ የሚደረጉ አሉ፡፡
ስፓርታ ፕራግ ከኢንተር ሚላን፣ ፌይኖርድ ከባየርን ሙኒክ፣ ሚላን ከጅሮና፣ ፒ.ኤስ.ጂ ከማንቸስተር ሲቲ፣ ሪያል ማድሪድ ከአር. ቢ ሳልዝቡርግ እና ሴልቲክ ከያንግ ቦይስ ይጫወታሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!