አጫጭር የዝውውር መረጃዎች።

0
217

ባሕር ዳር: ጥር 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አርሰናል የ25 ዓመቱን ማቲያስ ኩኛን በጥር የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ጠንካራ ፍላጎት እንዳለው እየገለጸ ይገኛል።

ቼልሲ በበኩሉ አርጀንቲናዊውን የክንፍ መስመር ተጫዋች አሌሃንድሮ ጋርናቾ ያስፈልገኛል እያለ ነው። ይህንም ፍላጎቱን ለማሳካት ከክለቡ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር እየተነጋገረ ነው። ተጫዋቹንም ለማዛወር 50 ሚሊዮን ዩሮ እንዳቀረበ ከቴሌግራፍ ሰምተናል።

ዩናይትዶች በዚህ የውድድር ዓመት ካሳዩት ደካማ አቋም ለመውጣት የቦርንማውዝን ሚሎስ ኬርኬዝ፣ የዎልቭስን ራያን አይት ኑሪ እና የክሪስታል ፓላስን ታይሪክ ሚቼልን ለማስፈረም ጥያቄ ማቅረባቸው ነው እየተነገረ የሚገኘው።

የዌስትሃም አዲሱ አሠልጣኝ ግርሃም ፖተርን ክለባቸውን ለማጠናከር ከዚህ የዝውውር ጊዜ በፊት የመሐል ተከላካይ እና የመሐል አጥቂ እያፈላለጉ እንደሚገኙ ኢንሳይደር አስነብቧል።

ቼልሲ ፈረንሳዊውን አጥቂ ክሪስቶፈር ንኩንኩን ለባየር ሙኒክ ለመልቀቅ 70 ሚሊዮን ፓውንድ መጠየቁን ስካይ ስፖርት ዘግቧል።

ማንቸስተር ሲቲ የመሐል ተከላካዩን ጁማ ባህን ከላሊጋው ክለብ ሪያል ቫላዶሊድ ለመውሰድ የቃል ስምምነት መጨረሳቸውን ፋብሪዞ ሮማኖ አስነብቧል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here