ፋሲል ከነማ እና መቻል ነጥብ ተጋርተዋል።

0
195

ባሕር ዳር: ጥር 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በ15ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ የዛሬ ጨዋታ ፋሲል ከነማን ከመቻል ጋር አገናኝቷል፡፡

በጨዋታውም ከእረፍት በፊት መቻል በ38ኛው ደቂቃ በበረከት ደስታ ግብ መርቷል። ከእረፍት መልስ ተጭነው የተጫዎቱት ፋሲል ከነማዎች በ70ኛው ደቂቃ በአንዋር ሙራድ ጎል አቻ ሁነው ጨዋታው 1ለ1 ተጠናቅቋል።

የጨዋታውን ውጤት ተከትሎ ፋሲል ከነማ በ17 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ሲቀመጥ መቻል በ26 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ መቀመጥ ችሏል።

በ15ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምር ሊግ ሌላው የተካሄደው ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ እና በውልዋሎ አዲግራት መካከል ሲኾን ጨዋታውም በተመሳሳይ 1ለ1 ተጠናቅቋል።

የሀዋሳ ከተማን ጎል በ47ኛው ደቂቃ እስራኤል እሸቱ ሲያስቆጥር የውልዋሎ አዲግራትን ጎል ደግሞ በ25ኛው ደቂቃ ናትናኤል ዘለቀ አስቆጥሯል።

የደረጃ ሠንጠረዡን በ26 ነጥብ የኢትዮጵያ መድኅንን፣ ሀዲያ ሆሳዕና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here