ባሕር ዳር: ጥር 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ እንግሊዛዊውን አማካይ ጄሚ ጊተንስን ለማስፈረም ጥረት እያደረጉ ነው።
ማንቸስተር ሲቲ ብራዚላዊውን የ26 ዓመቱን አማካኝ ዳግላስ ሉዊዝን ከጁቬንቱስ በውሰት ለማዘዋወር ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አትሌቲክ የተሰኘ ድረገጽ ዘግቧል።
የሪያል ማድሪዱን የፊት መስመር ተጫዋች ቪኒሲየስ ጁኒየርን ለመውሰድ የሳዑዲ አረቢያ ክለቦች ጥረት እያደረጉ ስለመኾኑ የስፔን የመገናኛ ብዙኀን እየዘገቡ ነው።
ቼልሲዎች እንግሊዛዊው የመሀል ተከላካይ ትሬቮህ ቻሎባህ ለክሪስታል ፓላስ ለመሸጥ 40 ሚሊዮን ፖውንድ እንደሚፈልጉ መግለጻቸውን ዘሰን አስነብቧል።
የ24 ዓመቱ ብራዚላዊ የክንፍ ተጫዋች አንቶኒ ማንቸስተር ዩናይትድን በመልቀቅ ወደ ላሊጋው ክለብ ሪያል ቤቲስ በውሰት ለመዛወር ከስምምነት ላይ መድረሱን ፋብሪዚዎ ሮማኖ አስነብቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!