ዛሬ ምሽት በኦልድ ትራፎርድ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ሳውዛሀምፕተን ይጫወታሉ፡፡

0
188

ባሕር ዳር: ጥር 08/2017 ዓ.ም(አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ፡፡ ምሽት አምስት ሰዓት በኦልድትራፎርድ ስታዲየም ማንቸስተር ዩናይትድ እና ሳውዛሀምፕተን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ዩናይትዶች እስካሁን ካደረጓቸው 20 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት በስድስቱ ብቻ ነው፡፡ በዘጠኝ ጨዋታዎች ተረትተዋል፡፡ 23 ነጥብ በመያዝም 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ በዛሬው ጨዋታ 85 በመቶ የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቷቸዋል፡፡

ቅዱሳኖቹ በበኩላቸው ካደረጓቸው 20 ጨዋታዎች በ16ቱ ተሸንፈው በሦስቱ ደግሞ አቻ ወጥተዋል። በአንዱ ብቻ በማሸነፍ እና ስድስት ነጥብ በመያዝ 20ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

በሌላ ጨዋታ ምሽት 4:30 ላይ በሊጉ 17ኛ ደረጃ የሚገኘው ኢፕስዊች ታውን 11ኛ ደረጃ ከተቀመጡት ብራይተኖች ጋር እንደሚጫወቱ ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here