ዛሬ የወጡ የዝውውር ወሬዎች፦

0
280

ባሕር ዳር: ጥር 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ግብጻዊ አጥቂ ሞሃመድ ሳላህ በክረምቱ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመውሰድ ማሳመኛ የሚኾን 65 ሚሊዮን ዩሮ ቀርቦለታል። አርሰናል የአጥቂ ክፍሉን ለማጠናከር በማሰብ የተለያዩ አማራጮችን እያጤነ ነው። የ26 ዓመቱን ስዊድናዊ አጥቂ ቪክቶር ጂዮከርስ እና የካሜሩን አጥቂ ብራያን ምቦሞን ለማስፈረም ጥረት እያደረጉ ነው።

ናፖሊ የ27 ዓመቱን እንግሊዛዊ እና የማንቸስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጫዋች ማርከስ ራሽፎርድን ለማስፈረም ፉክክር ውስጥ ገብቷል። ቼልሲ፣ ቶተንሃም እና ዌስትሃም ማርከስ ራሽፎርድን በውሰት ለመውሰድ ፍላጎት አሳይተዋል። ብራይተን የቼልሲ ንብረት የኾነውን የ27 ዓመቱን እንግሊዛዊ የመሐል ተከላካይ ቶሲን አዳራቢዮን ለማስፈረም ጥረት ጀምረዋል።

የቦርንማውዝ የግራ መስመር ተከላካይ ሚሎስ ኬርኬዝ ከማንቸስተር ሲቲ እና ከማንቸስተር ዩናይትድ ይልቅ ወደ ሊቨርፑል መሄድን እንደሚመርጥ ተገልጿል። ቼልሲዎቹ ለተከላካዩ ዝውውር 50 ሚሊዮን ዩሮ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ስፔናዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች ዬሬማይ ሄርናንዴዝ ከቼልሲ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን ሜትሮ ዘግቧል።

ማንቸስተር ዩናይትዶች ብራዚላዊውን የክንፍ መስመር ተጫዋች አንቶኒን እንደማይፈልጉት እና በዚህ የዝውውር ወቅት ተጫዋቹን ሪያል ቤቲስን ጨምሮ ከበርካታ ክለቦች ጋር እየተወያዩ እንደኾነም ነው እየተገለጸ ያለው። ቼልሲዎች የ24 ዓመቱ እንግሊዛዊ ተከላካይ ማርክ ጉሂን ከክሪስታል ፓላስ ለመውሰድ እያደረጉት ያለው ጥረት ላይሳካ እንደሚችል ነው የተዘገበው።

ኒውካስል ዩናይትድ እንግሊዛዊውን ተከላካይ ሎይድ ኬሊን ከፌነርባቼ ለመውሰድ ያቀረበው የ11 ሚሊዮን ፓውንድ ጥያቄ ውድቅ እንደተደረገበት አትሌቲክስ የተሰኘ ገጽ አስነብቧል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here