በእንግሊዝ ደርቢ የዛሬ የአርሰናል ጨዋታ ተጠባቂ ነው ።

0
612

ባሕር ዳር: ጥር 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 21ኛ ሳምንት አርሰናል ከቶተንሃም ሆትስፐር የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል። በ40 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው አርሰናል ዛሬ በሜዳው ቶተንሃም ሆትስፐርን ጋብዞ ጨዋታውን ያደርጋል።

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ታላላቆቹ ክለቦች አቻ እየወጡ ባለበት በዚህ ወቅት አርሰናል ዛሬ በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከኾነ በደረጃ ሠንጠረዡ ሁለተኛ ከመቀመጥም ባለፈ መሪው ሊቨርፑልን ይበልጥ ለመጠጋት ያስችለዋል።

መድፈኞቹ ባለፉት ጊዜያት ያደረጋጓቸውን ተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች እያሸነፉ በመምጣታቸው ጨዋታውን የማሸነፍ ይበልጥ ግምት ተሰጥቷቸዋል። ተጋጣሚው ቶተንሃም ሆትስፐር በተከታታይ ካደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች አንዱን አቻ ሲለያይ አንዱን ደግሞ ተሸንፏል። ይህም ቡድኑ ካለው ወቅታዊ አቋም በመነሳት ጨዋታው ሊከብደው ይችላል ነው የተባለው።

ቡድኖቹ እስካሁን 193 ጊዜ ተገናኝተዋል። 80 ጊዜ አርሰናል 61 ጊዜ ቶተንሃም ሆትስፐር ሲያሸንፉ 52 ጊዜ አቻ ተለያይተዋል። የዛሬው ጨዋታ ምሽት 5 ሰዓት ይካሄዳል። የዛሬውን ጨዋታ እንደጎርጎሳውያኑ ዘመን በ2006 የተገነባው 60 ሺህ 335 ሰዎችን የመያዝ አቅም ያለው ኢምሬት ስታዲየም ያስተናግዳል።

በሌሎች የ21ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ሲካሄዱ ኤቨርተን ከአስቶንቪላ፤ ሌስተር ሲቲ ከክሪስታል ፓላስ፤ ኒውካስል ዩናይትድ ከ ዎልቨርሃምፕተን ጋር ምሽት 4 ሰዓት ይጫዎታሉ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here