የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ የዛሬ ጨዋታዎች

0
520

ባሕር ዳር: ጥር 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ ጨዋታ ፉክክሩ አጓጊ ኾኖ ቀጥሏል። መቻል መሪነቱን ይበልጥ ለማጠናከር ዛሬ ወሳኝ ጨዋታ ያደርጋል። 14ኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ ሲቀጥል በአንድ ነጥብ ልዩነት የደረጃ ሠንጠረዡን እየመራ ያለው መቻል ያለውን ልዩነት ለማስፋት የሚያስችለውን ጨዋታ ነገ ያደርጋል።

መቻል ከደሬዳዋ ከተማ ጋር ነው 12:00 ሰዓት ላይ የሚጫወተው። በዚህ ጨዋታ ከሁለቱ ቡድኖች ወቅታዊ አቋም አንጻር ጨዋታው ለመቻል እንደማይከብደው ይገመታል። የመቻልን ወቅታዊ አቋም ስንመለከት በቅርብ ካደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች ሦስቱን አሸንፏል። በአንዱ ሲሸነፍ በቀሪው ነጥብ ተጋርቷል።

ድሬዳዋ ከተማ በበኩሉ በቅርቡ ከአደረጋቸው ጨዋታዎች በአራቱ ተሸንፏል። በአንዱ ደግሞ ሙሉ ነጥብ አሳክቷል። የዛሬው ጨዋታም ከመቻል ጥንካሬ ጋር ተደምሮ ሊቸገር እንደሚችል ተገምቷል። ቡድኖቹ ከዚህ በፊት 18 ጊዜ የመገናኘት ዕድል ነበራቸው ዘጠኝ ጊዜ መቻል ሲያሸንፍ ሁለት ጊዜ ድሬዳዋ ከተማ አሸንፏል። ሰባት ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።

መቻል፣ ሀድያ ሆሳዕና እና ባሕርዳር ከተማ በአንድ ነጥብ ተበላልጠው የደረጃ ሠንጠረዡን እየመሩ ነው። መቻል በ24 ነጥብ ነው እየመራ የሚገኘው።

መብራት ኀይል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 9:00 ሰዓት የሚያደርጉት የሊጉ ሌላው የዛሬ ጨዋታ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here