የዝውውር መረጃዎች፦

0
200

ባሕር ዳር: ጥር 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የ34 ዓመቱ እንግሊዛዊ የቀኝ መስመር ተከላካይ ካይል ዎከር ከኤሲ ሚላን ጋር የሁለት ዓመት ተኩል ኮንትራት ሊፈራረም መኾኑን ቴሌግራፍ አስነብቧል። ተጫዋቹ ምንአልባትም በሚቀጥሉት ቀናት ከማንቸስተር ሲቲ ሊለቅ እንደሚችል ነው እየተነገረ ያለው።

የሳኡዲ ፕሮ ሊግ ቡድኖች ዎከርን መፈለጋቸው አሁንም ቀጥሏል ነው የተባለው። ተጨዋቹ ግን በአውሮፓ የመቆየት ፍላጎት እንዳለው ነው ስካይ ስፖርት የዘገበው። የናፖሊው አሠልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ የ20 ዓመቱ የማንቸስተር ዩናይትድ የክንፍ መስመር ተጫዋች አሌሃንድሮ ጋርናቾን እንደሚፈልጉ ነው እየወጡ ያሉ መረጃዎች የሚያሳዩት።

የ23 ዓመቱ ጆርጂያዊ የክንፍ ተጫዋች ካቪቻ ካቫራታስኪሊያ ወደ ፓሪስ ሴንት ዠርሜይን ሊዘዋወር ይችላል መባሉን ተከትሎ ተጫዋቹን ለመተካት አሠልጣኙ ምርጫ ጋርናቾ ኾኗል። ከጁቬንቱስ ጋር ስሙ ሲያያዝ የቆየው ኡራጓዊ ተከላካይ ሮናልድ አውሮሃ ባርሴሎናን መልቀቅ እንደሚፈልግ እየተናገረ ባለበት በዚህ ወቅት የካታላኑ ክለብ የ25 ዓመቱን ተጫዋች ለማቆየት ጥረት እያደረገ ነው ተብሏል።

የ36 ዓመቱ ጀርመናዊ ተከላካይ ማትስ ሀምልስ በሮማ ለመቆየት የሚያስችለውን ፊርማ ለማኖር ብዙም እንደማይቸኩል ነው እየገለጸ ያለው። ዌስትሀም የብራይተኑ ኢቫን ፈርጉሰንን እና የማንቸስተር ዩናይትዱን አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድን በውሰት ለማዛወር ፍላጎት መኖሩን ቲቢአር አስነብቧል።

ባየር ሙኒክ ለካናዳዊው ተከላካይ አልፎንሶ ዴቪስ ዝውውር 25 ሚሊዮን ዩሮ ማቅረቡን ማርካ አስነብቧል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here