አማድ ዲያሎ በማንቸስተር ዩናይትድ ውሉን አራዘመ።

0
271

ባሕር ዳር: ጥር 1/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አማድ ክለቡ ማንቸስተር ዩናይትድ አስቸጋሪ የውድድር ጊዜ እያሳለፈ ቢኾን በግሉ ጥሩ ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል። በ27 ጨዋታዎች ስድስት ግቦችን አስቆጥሯል። የተጫዋቹ ውል በውድድር ዓመቱ ይጠናቀቅ ነበር። አሁን የፈረመው ውል ግን ኮትዲቯራዊን ለቀጣይ አምስት ዓመታት በኦልድ ትራፎርድ ያቆየዋል።

ክለቡ ከተቀናቃኞቹ ማንቸስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል ጋር በነበረው ጨዋታም ግብ ማስቆጠሩ በክለቡ ደጋፊዎች ዘንድ በአጭር ጊዜ እንዲወደድም አድርጎታል።

አማድ ከጣሊያኑ አታላንታ ከአራት ዓመት በፊት ነበር ዩናይትድ የተቀላቀለው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here