ኤቨርተን አሠልጣኙን አሰናበተ።

0
191

ባሕር ዳር: ጥር 1/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የእንግሊዙ ክለብ ኤቨርተን አሠልጣኝ ሲንዲያችን አሰናብቷል።

በየዓመቱ ወረደ ሲባል እንደምን የሚተርፈው የመርሲሳይዱ ክለብ በኤፍኤካፕ ከፒተርፕራህ ጋር ለመጫወት ሰዓታት ሲቀሩት አሠልጣኙን ማሰናበቱ እያነጋገረ ነው።

ክለቡ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በ19 ጨዋታ 17 ነጥብ በመያዝ 16ኛ ደረጃን ይዞ ይገኛል። ኤቨርተን አሠልጣኙ የተባረሩት በድንገተኛ ምክኒያት ነው ማለቱን ቢቢሲ በስፖርት ገጹ አስነብቧል።

ክለቡ ምሽት 4:45 የሚደረገውን የኤፍኤካፕ ጨዋታ የክለቡ የከ18 ዓመት በታች አሠልጣኝ ሌይተን ቤንስ እና የክለቡ አምበል ሽምስ ኮልማን እንዲመሩት ክለቡ ወስኗል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here