እግር ኳስዜናየውጭ ስፖርት ዌስትሃም ግርሃም ፖተርን አሠልጣኝ አደረገ። By Walelign Kindie - January 9, 2025 0 183 FacebookTwitterPinterestWhatsApp የእንግሊዙ ዌስትሃም ስፔናዊ ጁሊያን ሊፕቴጌን አሰናብቶ ፖተርን ቀጥሯል። ዌስትሃም በስፔናዊ አሠልጣኝ ውጤታማ መኾን አልቻለም። ይህን ተከትሎ ሊፕቴጌን ማሰናበቱ ይታወሳል። በእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ ከ20 ጨዋታ 23 ነጥብ በመሰብሰብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ግራሃም ፖተር በዌስትሃም ለሁለት ዓመት ተኩል ለመቆየት ነው የፈረሙት። ግራሃም ፖተር በቼልሲ እና በብራይተን በማሰልጠን አሳልፈዋል።