ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዎልቭሱ የፊት መስመር ተጫዋች ማታያስ ኩንያ ከኢፕስዊች ደኅንነት ጋር በገባው ግጭት በእግር ኳስ ማኅበሩ በሁለት ጨዋታዎች ታግዷል። ብራዚላዊው አጥቂ የኢፕስዊች የደኅንነት አባል የኾነውን መነፅር ከፊቱ ላይ ከመንጠቁ በተጨማሪ በክርን በመምታት በፈጸመው የሥነ ምግባር ጉድለት ነው ለቅጣት የተዳረገው።
የእግር ኳስ ማኅበሩ ከጨዋታ ቅጣት በተጨማሪ የ80 ሺህ ፓውንድ ቅጣት ጥሎበታል።
የ25 ዓመቱ ኩንያ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በ19 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች 10 ጎሎችን ለክለቡ ዎልቭስ ማስቆጠር የቻለ ተጫዋች ነው፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!