ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ 18ኛ ሳምንት የበዓል ሰሞን ጨዋታ ዛሬ አርሰናልን ከኢፕሲዊች ታውን ያገናኛል፡፡
ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን በማሸነፍ የተሻለ ወቅታዊ አቋም ያለው አርሰናል በዛሬው ጨዋታ አሸንፎ የፕሪምርሊጉ መሪ ሊቨርፑልን ለመጠጋት እና ከተከታዩ ቸልሲ በደረጃ ሠንጠረዡ በልጦ ለመቀመጥ የዛሬውን አጋጣሚ ይጠቀማል ወይ? የሚለው የዚህ ጨዋታ ውጤት ተጠባቂ እንድኾን አድርጎታል፡፡
ታላላቆቹ የእንግሊዝ ክለቦች ነጥብ እየጣሉ ባለበት በዚህ ወቅት ከአምስት ጨዋታዎች ሦስቱን በማሸነፍ እና ሁለቱን አቻ በመለያየት የተሻለ የሚባለው አርሰናል ጨዋታውን የማሸነፍ ግምት ተሰጥቶታል፡፡
ከአምስት ተከታታይ ጨዋታዎች አራቱን ተሸንፎ በአንዱ ብቻ ያሸነፈው ተጋጣሚው ኢፕሲዊች ታውን አርሰናልን ይቋቋማል ተብሎ አልተገመተም።
ይሁን እንጅ እንደ ሳካ እና ዋይት ያሉ ተጫዋቾቹን ጨምሮ ሌሎች ተጫዋቾቹን በጉዳት የማያሰልፈው አርሰናል እንደተገመተው ላይኾን የሚችልበት አጋጣሚም ሊኖር እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡
በተጋጣሚው በኩልም ስድስት ተጫዋቾች በጉዳት እንደማይሰለፉ ታውቋል፡፡ 58 ጊዜ የተገናኙት ሁለቱ ቡድኖች 30 ጊዜ አርሰናል ሲረታ 18 ጊዜ ተጋጣሚው ኢፕሲዊች ታውን አሸንፏል፣ 10 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል፡፡
በሌላ የበዓል ሰሞን መርሐ ግበር ብራይተን ከብሬንትፎርድ ምሽት 4፡30 የሚገናኙ ይኾናል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!