ማንቸስተር ዩናይትድ ከዎልቭስ ጋር ያደረገውን ጨዋታ ተሸነፈ።

0
172

ባሕር ዳር: ታኅሳስ 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ማንችስተር ዩናይትድ ከዎልቭስ ጋር ያደረገውን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የበዓል ሰሞን መርሐ ግብር 2 ለ 0 በኾነ ውጤት ተሸንፏል። የዎልቭስን የማሸነፊያ ግብ ህዋንግ እና ኩንሀ አስቆጥረዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በውድድር ዘመኑ ስምንተኛ የፕርሚየር ሊግ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

ፖርቹጋላዊው አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ በውድድር ዓመቱ በሁሉም ውድድሮች ሦስተኛ ቀይ ካርዱን ተመልክቷል።

ፈርናንዴዝ ከ19 ዓመታት በኋላ በአንድ የውድድር ዘመን ሦስት ቀይ ካርድ የተመለከተ የመጀመሪያው የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ኾኗል።

ማኑኤል ኡጋርት የማስጠንቀቂያ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ በቅጣት ምክንያት ቀጣዩ የኒውካስል ዩናይትድ ጨዋታ የሚያመልጠው ይኾናል።

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝነታቸው አምስተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here