ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የብሔራዊ ስታዲዮም የግንባታ ሂደት አፈጻጸም በከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገምግሟል። በምግምገማው የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ እና የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ መኪዩ መሐመድ የብሔራዊ ስታዲዮም የግንባታ ሂደት አፈጻጸም ሪፖርትን በመገምገም ምልከታ አድርገዋል።
የፕሮጀክቱን ሥራዎች እያከናወነ የሚገኘው ተቋራጭ የተከናወኑ፣ እያከናወነ ያለውን የፊዚካል እና የቴክኒካል ሥራዎች አፈጻጸም ሪፖርትን በማቅረብ በከፍተኛ መሪዎች ግምገማ ተደርጎበታል ነው የተባለው። የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ ፕሮጀክቱ ከተያዘለት ጊዜ በፊት መጠናቀቅ እንዳለበት አቅጣጫ ሰጥተዋል ተብሏል።
ከባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ተቋራጩ ለቀሪ ሥራዎች የሚኾኑ እቃዎችን በማስገባት ላይ መኾኑ ተገልጿል። ከዚህ በኋላ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም እድገት እንደሚኖረውም ተመላክቷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!