በቻን የማጣሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሱዳን ጋር ከደቂቃዎች በኋላ ይጫወታል።

0
126

ባሕር ዳር: ታኅሳስ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ቡድኑ በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ 2 ለ 0 መሸነፉ ይታወሳል። በዛሬው ጨዋታ ይህን ውጤት ቀልብሶ ለቻን ለማለፍ ከፍተኛ ጥረት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

አሠልጣኝ መሳይ ተፈሪ በጨዋታው የመጀመሪያ 11 ተሰላፊዎችን አሳውቀዋል። በዚህ መሰረት ግብ ጠባቂ ሰይድ ሐብታሙ፣ ተከላካዮች አማኑኤል ተረፉ፣ ያሬድ ባየህ፣ ራምኬል ጀምስ እና አስራት ቱንጆ ናቸው።

የመሃል ሜዳ ተሰላፊዎች በረከት ወልዴ፣ አማኑኤል ዮሃንስ፣ ያሬድ ካሳየ ሆነዋል።

የፊት መስመሩ ደግሞ አብዱልከሪም ወርቁ፣ በረከት ደስታ እና አማኑኤል ኤርቦ ይመሩታል።

ድል ለኢትዮጵያ!

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here