አጫጭር የዝውውር መረጃዎች

0
202

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሊቨርፑል የ23 ዓመቱን ብራዚላዊ የብራይተን የፊት መስመር ተጫዋች ጆኦ ፔድሮን ለማስፈረም የክረምቱ የዝውውር ጊዜን በመጠበቅ ላይ እንደኾነ ቢቢሲ በስፖርት ጭምጭምታ አምዱ አስነብቧል። በሌላ በኩል የ25 ዓመቱ ስዊዲናዊ አጥቂ የኒውካስትል ዩናይትድ ንብረት የኾነውን አሌክሳንደር ኢሳክ በፓሪስ ሴንት ዠርሜይን እየተፈለገ ነው። ከለቡ ተጫዋቹን ለማስፈረም 100 ሚሊዮን ዩሮ እንደቆረጠለት እየተነገረ ነው።

ፒኤስጂ የአትሌቲክ ቢልባኦን የክንፍ ተጫዋች ኒኮ ዊሊያምስን ኮንትራት ለማስፈረስ 48 ሚሊዮን ዩሮ ማቅረቡ ሲሰማ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ባርሴሎና የ22 ዓመቱን ስፔናዊ አጥቂ እንደሚፈልጉት ታውቋል እየተባለ ነው።

ባርሴሎና በኔዘርላንዱ አማካኝ ፍሬንኪ ዴ ጆንግ ላይ እምነት በማጣቱ የ27 ዓመቱን ተጫዋች የስፔኑን ክለብ የመልቀቅ ዕድሉ ከፍ ማለቱ እየተነገረም ይገኛል።

ሌስተር ሲቲ አርጀንቲናዊውን የመሐል ሜዳ ተጫዋች ቫለንቲን ጎሜዝን ከቬሌዝ ሳርስፊልድ ለማስፈረም 8 ሚሊዮን ፓውንድ አቅርቧልም ተብሏል።

ኒውካስትል የ23 ዓመቱን የባርሴሎና ተጨዋች ኤሪክ ጋርሺያን ለማስፈረም ፍላጎት ያለው ቢኾንም ተጫዋቹ በኑ ካምፕ መቆየት እንደሚፈልግ ነው የተገለጸው።

ክሪስታል ፓላስ በበኩሉ የቤኔፊካውን ጀርመናዊ አማካኝ ጃን-ኒክላስ ቤስቴን በጥር ማስፈረም ይፈልጋል ተብሏል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here