ቪኒሺየስ ጁኒየር የፊፋ ምርጥ ተጫዋች በሚል ተመርጧል፡፡

0
163

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሪያል ማድሪዱ ተጫዋች ቪኒሺየስ ጁኒየር የ2024 የፊፋ ምርጡ ተጫዋች በሚል ተመርጧል፡፡

ተጫዋቹ የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች የተባለው በኳታር ዶሀ በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ነው።

የ24 ዓመቱ ብራዚላዊ ተጫዋች በ2023/24 የውድድር ዘመን ለሪያል ማድረድ 24 ግቦችን ሲያስቆጥር 11 ግብ የሚኾኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።

በአሠልጣኞች ዘርፍ የሪያል ማድሪዱ አሠልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የፊፋ የዓመቱ ምርጥ አሠልጣኝ በመኾን ተመርጠዋል፡፡

የባርሴሎናዋ አማካኝ አይታና ቦንማቲም የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ሴት ተጫዋች በመባል ተመርጣለች።

ይህ ምርጫ የሚወሰነው የብሔራዊ ቡድን አምበሎች 25 ከመቶ፣ የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኞች 25 ከመቶ፣ በተመሳሳይ ጋዜጠኞች እና ደጋፊዎች 25 ከመቶ በሚሰጡት ድምጽ እንደሚወሰን ቢቢሲ በስፖርት ገጹ አስነብቧል።

ዘጋቢ፦ ሃብታሙ ዳኛቸው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here