የቼልሲው ሚካሄሎ ሙድሪክ ከጨዋታ ታገደ።

0
228

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የ23 ዓመቱ ዩክሬናዊ የቼልሲ የክንፍ መስመር ተጫዋች ሚካሄሎ ሙድሪክ ከእግር ኳስ ጨዋታ ታገደ፡፡ ተጫዋቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከለከለ አበረታች ንጥረ ነገር ተጠቅሟል በሚል ነው የታገደው፡፡

የእንግሊዝ እግር ኳስ ማኅበርም የሚካሄሎ ሙድሪክን እገዳ በቋሚነት ለማጽናት ወይም ለመሻር ምርመራውን አጠናክሮ ቀጥሎበታል ሲል ቢቢሲ አስነበቧል፡፡

ተጫዋቹ በኢንስታግራም ገጹ ላይ “ምንም ዓይነት የተከለከለ ንጥረ ነገርን ተጠቅሜ አላውቅም፤ ምንም ስህተት እንዳልሠራሁ አውቃለሁ፤ እናም በቅርቡ ወደ ሜዳ እንደምመለስ ተስፋ አደርጋለሁ” በማለት አስተባብሏል፡፡

ሙድሪክ ከሻክታር ዶኔስክ ቼልሲን የተቀላቀለው እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2023 ነበር፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here