ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የተለያዩ የሴቶች ውድድሮች የዕጣ ማውጣት ሥነ ሥርዓት አከናውኗል። በዚህም ኢትዮጵያ በሦስት ውድድሮች ተጋጣሚዎቿን ለይታለች። የ2026 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣሪያ አንደኛ ዙር ዩጋንዳን ከኢትዮጵያ ያገናኛል።
የ2026 የአፍሪካ ዞን የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ሁለተኛ ዙር ላይ ኢትዮጵያ ከኬንያ ትገናኛለች።
የ2025 የአፍሪካ ዞን የሴቶች ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ አንደኛ ዙር ላይ ዚምባብዌ ከኢትዮጵያ ይገናኛሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!