ዛሬ የተደረጉ ሁለት የኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ።

0
197

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 1/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ በተካሄደው የኢትዮጵያ የፕሪሜርሊግ 11 ሳምንት ጨዋታ ወላይታ ዲቻ እና አዳማ ከተማን አገናኝቶ 2ለ2 በኾነ ውጤት ተጠናቅቋል። በዚህ ጨዋታ ዳምጠው እና ሰለሞን ለ ወላይታ ዲቻ ግብቹን ሲያስቆጥሩ በአዳማ ከተማ በኩል መንግሥቱ እና ኑሪ ጎሎችን አስቆጥረዋል።

በጨዋታው ብርሃኑ በቀለ የቢጫ ካርድ ከማየቱ ውጭ ዳኛው ካርዶችን አልመዘዙም። ጨዋታውን ለማሸነፍ ከነበረ ፍላጎት በመነጨ ወላይታ ዲቻ ሦስት ተጫዋቾችን ሲቀይሩ በአዳማ በኩል ሁለት ተጫዋቾችን ቀይረው ለመጫዎት ጥረት አድርገዋል። የጨዋታ ውጤትን ተከትሎ ወላይታ ዲቻ በ16 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ሲቀመጥ አዳማ ከተማ በ12 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ሌላው የተካሄደው ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና እና በውልዋሎ አዲግራት መካከል የተካሄደው ጨዋታ ያለምንም ግብ ተጠናቅቋል።በዚህ ጨዋታ በሁለቱም ቡድኖች ላይ ዳኛው ስድስት ቢጫ ካርድ መዘዋል። ኢትዮጵያ ቡና አራት ተጫዋች ሲቀይር ውልዋሎ አዲግራት ሁለት ተጫዋቾችን ቀይረው ለመጫወት ሞክረዋል።

በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ ቡና በ12 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ሲቀመጥ ውልዋሎ አዲግራት በአንድ ነጥብ የደረጃ ሠንጠረዡ ግርጌ ላይ ተቀምጧል።

የፕሪሜርሊጉን የደረጃ ሠንጠረዥ መቻል በ20 ነጥብ እየመራ ይገኛል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here