የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽንን ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚመሩ እጩዎች ይፋ ኾኑ፡፡

0
208

ባሕር ዳር: ኅዳር 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽንን ለቀጣይ አራት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት እና በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት የሚመሩ እጩዎች ይፋ ኾነዋል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ታኅሳስ 12 እስከ 13 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በሚያካሂደው 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ፌዴሬሽኑን ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚመሩ ፕሬዚዳንት እና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን እንደሚመረጥ ተመላክቷል፡፡

ክልሎች እና ከተማ አስተዳድሮች አትሌቲክስ ፌደሬሽኑን ቢመሩ ያሏቸውን እጩዎቻቸውን አሳውቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳመላከተው በእጩዎች ተገቢነት ላይ አስፈላጊው ማጣራት እየተካሄደ ነው፡፡

የአማራ ክልል ለኢትዮጵያ አትሌተክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳትነት አቶ ያየህ አዲስን በእጪኑት አቅርቧል፡፡ ለሥራ አስፈጻሚነት ደግሞ አቶ ቢልልኝ መቆያን እና ወይዘሮ አበባ ዮሴፍን በእጩነት ማቅረቡ ተመላክቷል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here