የሞ ሳላህ ቆይታ አለመረገጋገጥ እና የደጋፊዎች ስጋት

0
277

ባሕር ዳር: ኅዳር 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ግብጻዊ ሞ ሳላህ በሊቨርፑል ደጋፊዎች የሚዘመርለት ተጫዋች ነው። ክለቡ በክሎፕ ዘመን ለነበረው ውጤታማነት ከሚመሰገኑ ተጫዋቾች መካከል ነው።

ሊቨርፑል በአዲሱ አሠልጣኝ አርኔ ስሎት ዘንድሮ ድንቅ ግስጋሴ ላይ ይገኛል። ለዚህ ስኬት ደግሞ የግብጻዊ ኮከብ ምርጥ ብቃት ብዙ አግዞታል።

ሳላህ ሊቨርፑል በዚህ ዓመት በፕሪምየር ሊጉ ካስቆጠራቸው 24 ግቦች በ16 ተሳትፎ አድርጓል። በሁሉም ውድድሮች 18 ጨዋታዎች ደግሞ 12 ግቦችን አስቆጥሮ 10 ግብ የኾኑ ኳሶቹን አቀብሏል።

እነዚህ ቁጥሮች ሳላህ በአንፊልድ በቀላሉ የማይተካ ተጫዋች መኾኑን ያሳያሉ። ነገር ግን የተጫዋቹ የቀዮቹ ቤት ቆይታ በመጭው ሰኔ ይጠናቀቃል። ይህ ለደጋፊዎቹ ትልቅ ስጋት ኾኗል።

ሊቨርፑል እና ሳላህ በኮንትራት ማራዘም ዙሪያ የገፋ ንግግር አለማድረጋቸው ደግሞ ተጫዋቹ በሊቨርፑል የመጨረሻ ጊዜው ላይ እንደሚገኝ የሚጠቁም ኾኗል።

በፕሪምየር ሊጉ 12ተኛ ሳምንት ሳውዝፕተንን ሊቨርፑል 3 ለ 2 አሸንፏል። በዚህ ወቅት የተወሰኑ ደጋፊዎች ክለቡ የሞ ሳላህን ውል እንዲያራዝም የሚጠይቁ ጽሑፎችን ሜዳ ላይ ይዘው ተገኝተዋል። በጨዋታው ግብጻዊ ተጫዋች ሁለት ግቦችን ማስቆጠሩ ይታወሳል።

ሳላህ ከዚህ በፊት ቆይታውን በተመከተ በሊቨርፑል የመጨረሻ ዓመቱ ሊኾን እንደሚችል መናገሩን ጎል የመረጃ ምንጭ አስታውሷል።

የሳኡዲ ክለቦች ሳላህን በከፍተኛ ደሞዝ ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው በየጊዜው የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here