ባሕር ዳር: ኅዳር 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ)
የአውሮፓ ሀገራት በእግር ኳስ ደረጃቸው በተለያዩ ቋቶች ተከፋፍለው የኔሽንስ ሊግ ጨዋታዎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል።
በመጀመሪያው ቋት የሚገኙት በእግር ኳስ ደረጃቸው መጀመሪያ ላይ የሚጠቀሱት ናቸው። እነዚህ ሀገራት መካከል ከሰሞኑ በተደረጉ ጨዋታዎች ለሩብ ፍጻሜ የበቁት ተለይተዋል።
ለሩብ ፍጻሜ የበቁት ስምንቱ ሀገራት ግማሽ ፍጻሜ ለመድረስ ለሚደረገው ጨዋታ ተጋጣሚዎቻቸውን ለይተዋል።
በዚህ መሰረት ኔዘርላንድ ከስፔን፣ ክሮሽያ ከፈረንሳይ፣ ዴንማርክ ከፖርቱጋል እና ጣሊያን ከጀርመን ተደልድለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!