ፔፕ ጋርዲዮላ በሲቲ ቤት ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለመቆየት ተስማማ።

0
205

ባሕር ዳር: ኅዳር 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጋርዲዮላ የሲቲ ቆይታውን 10 ዓመት ለማድረስ አዲስ ውል ለመፈራረም መስማማቱን ቢቢሲ በስፖርት ገጹ አስነብቧል።

የ53 ዓመቱ ስፔናዊው ፔፕ ጋርዲዮላ በ2016 ሲቲን የተቀላቀለ ሲኾን እስካኹን 6 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ጨምሮ 18 ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል።

አሠልጣኙ በኢትሃድ ያለው ኮንትራት በያዝነው የውድድር ዘመን መጨረሻ ይጠናቀቃል። ይህን ተከትሎ ነው ጋሪዲዮላ ወሉን ለአንድ ተጨማሪ ዓመት ለማራዘም የተስማማው።

አሠልጣኙ ሲቲ በአንድ የውድድር ዘመን ማንቸስተር ሲቲ ፕሪምየር ሊግ፣ ኤፍኤ ካፕ እና ሻምፒዮንስ ሊግ በማንሳት በዩናይትድ ብቻ ተይዞ የነበረውን ታሪክ እንዲጋራ አግዟል።

በተከታታይ አራት ጊዜ የእንግሊዝ ፕሪምየር ዋንጫን በማንሳት እና 100 የፕሪምየር ሊግ ነጥቦችን በመሠብሠብም ክለቡ በፕሪምየር ሊጉ ታሪክ ባለክብረ ወሰን እንዲኾን ትልቅ ሚና ተጫውቷል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here