ባሕር ዳር: ኅዳር 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ)
የቀድሞው የቼልሲ ኮከብ ፍራንክ ላፓርድ ኮቨንትሪን ለማሠልጠን ንግግር ላይ መኾኑን ዘ ሰን ጽፏል።
ኮቨንትሪ በእንግሊዝ ቻምፒዮንስ ሺፕ እየተወዳደረ ያለ ቡድን ነው። ክለቡ በዚህ የውድድር ዘመን ካደረጋቸው 15 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አራቱን ብቻ ነው። ይህን ተከትሎ አሠልጣኙ ማርክ ሮቢንስ ተሰናብተዋል።
አሁን ፍራንክ ላምፓርድ ክለቡ በአዲስ አሠልጣኝነት እንደሚረከብ እየተጠበቀ ነው።
በተጫዋችነት ዘመኑ ድንቅ የእግር ኳስ ጊዜን ያሳለፈው እንግሊዛዊ ላምፓርድ በአሠልጣኝነት በቼልሲ፣ ኤቨርተን እና ደርቢ አሳልፏል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!