ሩድ ቫን ኒስትሮይ ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር በይፋ ተለያየ።

0
166

ባሕር ዳር: ኅዳር 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ)ሆላንዳዊው የቀድሞ የእግር ኳስ ኮከብ ሩድ ቫን ኒስትሮይ ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር በይፋ ተለያይቷል፡፡

የ48 ዓመቱ የቀድሞ የማንቼስተር ዩናይትድ ኮከብ በሁለት ዓመት የኮንትራት ውል የማንቼስተር ዩናይትድ ምክትል አሰልጣኝ ለመኾን መስማማቱ ይታወሳል፡፡

የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግን ስንብት ተከትሎም ቫን ኒስትሮይ ማንቼስተር ዩናይትድን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት እየመራ ሦስት ጨዋታዎችን ማሸነፍ ችሏል፡፡

አዲሱ የማንቼስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ በመኾን የተሾሙት ሩበን አሞሪም በራሳቸው የአሰልጣኝ ቡድን (ኮቺንግ ስታፍ )አባላት ቡድኑን ለማዋቀር መፈለጋቸውን ተከትሎ ቫን ኒስትሮይ በይፋ ከክለቡ ጋር ተለያይቷል፡፡

ማንቼስተር ዩናይትድ የኮከቡን ስንበት ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ሩድ ቫን ኒስትሮይ ሁልጊዜም የማንቼሰትር ዩናይትድ ባለታሪክ ኾኖ ይቀጥላል ብሏል፡፡

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ቫን ኒስትሮይ በአምስት የውድድር ወራት ውስጥ ላበረከተው አስተዋፅኦም ክለቡ ምስጋና አቅርቧል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here