ባሕር ዳር: ጥቅምት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ስፔናዊው ውጤታማ አሠልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በሲቲ ቤት ከዚህ በላይ ለረጅም ዓመታት የመቆየት ፍላጎት እንደሌላቸው በተደጋጋሚ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ይህን ተከትሎ የማንቸስተሩ ክለብ ጋርዲዮላ በቃኝ ሲሉ እሳቸውን የሚተካ ጥሩ አሠልጣኝ ማን ይኹን በሚለው ዙሪያ እያሰበበት መኾኑን ዘገባዎች አመላክተዋል።
ዘአትሌቲክ የተሰኘው የመረጃ ምንጭ ሲቲ በቀጣይ ለመቅጠር እያሰባቸው ካሉ አሠልጣኞች መካከል ዣቪ አሎንሶ ቀዳሚው ነው ሲል ጽፏል። አሎንሶ በባየር ሊቨርኩሰን ያሳየው ድንቅ ሥራ በሊቨርፑል እና ባየርሙኒክ ተፈላጊ አድርጎት ነበር። ነገር ግን የሁለቱን ክለቦች ጥያቄ ውድቅ በማድረግ በሊቨርኩሰን ቀጥሏል።
አሁን ደግሞ የስኬታማው ጋሪዲዮላ ተተኪ እንዲኾን ታስቧል። ከአሎንሶ በተጨማሪ ሌሎች አሠልጣኞችንም በአማራጭነት እያየ ያለው ሲቲ ትልቁ ትኩረቱ ግን ፔፕ ጋሪድዮላን ለረዥም ዓመታት ማቆየት ነው ተብሏል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!