ባሕር ዳር: ጥቅምት 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በ35 ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ የሚደረጉ ጨዋታዎች እንደቀጠሉ ናቸው። ምድብ ስምንት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያም ጨዋታዎችን እያከናወነች ነው። በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው የአሠልጣኝ ገብረ መድን ሀይሌ ሥብሥብ ዛሬ ከጊኒ ጋር ይጫወታል።
ቡድኑ ቀደም ብሎ ባደረጋቸው ሦሥት ጨዋታዎች ማግኘት የቻለው አንድ ነጥብ ብቻ ነው። በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይም ይገኛል። ተጋጣሚዋ ጊኒ ደግሞ በተመሳሳይ የጨዋታ ቁጥር ሦሥት ነጥብ በመያዝ የምድቡ ሦሥተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ምድብ ስምንትን በሦሥት ጨዋታ ዘጠኝ ነጥብ የሠበሠበችው ዲሞክራቲክ ኮንጎ በቀዳሚነት እየመራችው ነው። ታንዛኒያ ደግሞ በአራት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
በዚሁ ምድብ ዛሬ ታንዛኒያ ዲሞክራቲክ ኮንጎን ትገጥማለች። በተመሳሳይ በሌሎች ምድቦችም ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። ኮሞሮስ ከቱኒዚያ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ከሞሮኮ፣ ሞሪታኒያ ከግብጽ፣ ሩዋንዳ ከቤኒን፣ ሱዳን ከጋና፣ ማላዊ ከሴኔጋል፣ ኮንጎ ከደቡብ አፍሪካ ከጨዋታዎቹ መካከል የሚጠበቁት ናቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!