“በፓራሊምፒክ ጨዋታዎች ለሚሳተፈው ሉዑክ አስፈላጊው ድጋፍ እና ማበረታቻ ይደረጋል”የባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር

0
244

ባሕር ዳር: ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በፓሪስ በሚደረገው 17 ኛው የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ዛሬ አሸኛኘት እንደሚደረግለት የባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ከነሐሴ 22 እስከ ጳጉሜን 3 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳሉ።

በውድድሩ ላይ ከ184 ሀገራት የተወጣጡ 4 ሺህ 400 አትሌቶች በ22 የስፖርት ዓይነቶች ይወዳደራሉ ተብሎ ይጠበቃል። ኢትዮጵያም በአትሌቲክስ ስፖርት ስድስት ተወዳዳሪዎችን ታሳትፋለች።

የባሕል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በውድድሩ ላይ የሚሳተፈውን የኢትዮጵያ ፓራሊምፒክ ልዑካን ቡድን አበረታተዋል። መንግሥት ለልዑኩ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ማበረታቻ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ዛሬ ከሰዓት በኋላ አሸኛኘት እንደሚደረግለት ከባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያ ከሦስት ዓመት በፊት በቶኪዮ በተካሄደው 16 ኛው የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች በአንድ የወርቅ ሜዳሊያ 59ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ የሚታወስ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here