ቡሩኖ ፈርናንዴዝ በዩናይትድ ውሉን አራዘመ።

0
372

ባሕር ዳር: ነሐሴ 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ፖርቱጋላዊ ቡሩኖ ፈርናንዴዝ ለማንቸስተር ዩናይትድ በግሉ ጥሩ ግልጋሎት እየሰጠ ነው። ቡድኑን በአምበልነት እየመራም ይገኛል። ነገር ግን ክለቡ በድሮው ልክ ውጤታማ አለመኾኑን ተከትሎ ፈርናንዴዝ ዩናይትድ ሊለቅ ይችላል የሚሉ ዜናዎች ተናፍሰው ነበር።

ነገር ግን ተጫዋቹ ለተጨማሪ ዓመታት በኦልድ ትራፎርድ ለመቆየት ከክለቡ ጋር ተስማምቷል። እንደ ኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ ፈርናንዴዝ እስከ 2027 ለመቆየት ተስማምቷል። እንደ አስፈላጊነቱ ተጨማሪ አንድ ዓመትም በውሉ ውስጥ ይገኛል።

ተጫዋቹ በዩናይትድ ከፍተኛ ገንዘብ ከሚያገኙ ተጫዋቾች መካከልም አንዱ ኾኗል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here