ማንቸስተር ዩናይትድ ሁለት ተከላካዮችን አስፈረመ፡፡

0
274

ባሕር ዳር: ነሐሴ 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ማንቸስተር ዩናይትድ ማቲያስ ዲላይት እና ኑሴር ማዝራዊን አስፈርሟል፡፡ እንግሊዛዊ ቢሊዬነር ሰር ጂም ራትክሊፍ ኦልድ ትራፎርድ ከደረሱ በኋላ በማንቸስተር ዩናይትድ ቤት በርካታ ለውጦች እየታዩ ነው፡፡ የክለቡን ድርሻ ከግሌዘር ቤተሰቦች የገዙት ቢሊኔሩ ማንቸስተርን ወደ ቀደመ ኃያልነቱ ለመመለስ እንደሚሠሩ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ሰውዬው እንዳሉትም በማንቸሰተር ዩናይትድ በርካታ ለውጦች እየታዩ ነው፡፡ ማንቸስተር ዩናይትድ በ2024/25 የተጨዋቾች የዝውውር ወቅት ብርቱ ተሳትፎ እያደረገ ነው፡፡ ከአሁን በፊት ጆሹዋ ዚርከዚ እና ሌኒ ዮሮን ያስፈረመው ማንቸሰተር ዪናይትድ ተጨማሪ ሁለት ተጨዋቾችን አስፈርሟል፡፡

የቀድሞዎቹ የባየርን ሙኒክ የተከላካይ መስመር ተጨዋቾች ዲላይት እና ማዝራዊ ከቀድሞ አሠልጠኛቸው ጋር ዳግም ለመሥራት ኦልድ ትራፎርድ ደርሰዋል፡፡ በአያክስ በአሠልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ ሥር የሠለጠኑት ሁለቱ የተከላካይ መስመር ተጨዋቸች በዩናይትድ ዳግም ተገናኝተዋል።

ቢበሲ በዘገባው ኔዘርላንዳዊ የመሐል ተከላካይ ማቲያስ ዲላይት በኦልትራፎርድ የሚያቆዬውን የአምስት ዓመት ውል ፈርሟል፤ ተጨዋቹ ለተጨማሪ አንድ ዓመት የማራዘም አማራጭ በውሉ ላይ ሰፍሯል ብሏል፡፡ ሞሮኳዊው ማዝራዊ ደግሞ በኦልድትራፎርድ ለአራት ዓመታት የሚያቆዬውን ውል ነው የፈረመው፡፡ እርሱም ተጨማሩ አንድ ዓመት ማራዘም የሚችልበት አማራጭ በውሉ ላይ ሰፍሯል፡፡ አሠልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ ለሁለቱ ተጨዋቾች እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ይነገራል፡፡

ሆላንዳዊ ተከላካይ ዲላይት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃንግ ለእግር ኳስ እድገቱ አስተዋጽዖአቸው ከፍ ያለ መኾኑን ተናግሯል፡፡ በድጋሜ ከእርሳቸወ ጋር የመሥራት እድል በማግኘቱ ደስተኛ መኾኑንም ገልጿል፡፡ ሞሮኳዊ ማዝራዊውም ከአሠልጣኙ ጋር ዳግም በመገናኘታቸው መደሰቱን አልደበቀም፡፡

እስካሁን ስኬታማ ዝውውር የፈጸመው ማንቸስተር ዪናይትድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ለማስፈረም በገበያው ላይ እያማተረ ነው፡፡ ኡራጋዊው የፒ ኤስ ጂ የመሐል ሜዳ ተጫዋች ማንኡል ኡጋርቴ ደግሞ ከማንቸስተር ዪናይትድ ጋር ስሙ በስፋት እየተያያዘ ነው፡፡ ተጨዋቾቹ በቃል ደረጃ ከማንቸሰተር ዩናይትድ ጋር መስማማቱም እየተነገረ ነው፡፡ ነገር ግን ሁለቱ ክለቦች በተጨዋቾቹ ዝውውር ዙሪያ ከስምምነት አልደረሱም፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here