በኦሎምፒክ ጨዋታዎች የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ።

0
239

ባሕር ዳር: ነሐሴ 07/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በፓሪስ በተካሄደው 33ኛው የኦሎምፒክ ጨዋታዎች የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብቷል።

ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የባሕል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ የሚኒስቴሩ የዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሥራ መሪዎች እና ሌሎች እንግዶች አቀባበል አድርገውለታል።

ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ እና ውኃ ዋና ስፖርት 38 ስፖርተኞችን አሳትፋለች። 1 የወርቅ እና 3 የብር አጠቃላይ 4 ሜዳሊያዎችን በማግኘት 47ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። በአትሌቲክስ የሜዳሊያ ሰንጠረዥም 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

በአቀባበል ሥነ ስርዓቱ የባሕል እና ስፖርት ሚኒስትሯ ሸዊት ሻንካ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። ሚኒስትሯ በፓሪስ ኦሎምፒክ ሀገርን ወክለው ብሔራዊ ኩራት ለመኾን ላሳዩት ብርቱ ጥረት ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይም የተሻለ ውጤት እንዲመጣ መንግሥት ድጋፍ ያደርጋልም ነው ያሉት።

ዛሬ ከቀኑ 10:30 ሰዓት ለልዑካን ቡድኑ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት የሽልማት እና የእውቅና መርሐግብር ይከናወናል ተብሎ ይጠበቃል።

ዘጋቢ:- ቴወድሮስ ኃይለኢየሱሥ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here