በፓሪሱ ኦሎምፒክ በወንዶች እግርኳስ ፈረንሳይ እና ስፔን ለወርቅ ሜዳልያ ዛሬ ይጫወታሉ።

0
214

ባሕር ዳር: ነሐሴ 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የፓሪሱ ኦሎምፒክ እየተገባደደ ነው። ውድድሮችም ፍጻሜ እያገኙ ነው። በእግር ኳስ ወንዶች ፈረንሳይ እና ስፔን ለፍጻሜ መድረሳቸው ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ የወርቅ ሜዳልያውን ለማጥለቅ ይጫወታሉ። ጨዋታውም ምሽት 1 ሰዓት ይደረጋል።

በግማሽ ፍጻሜ ፈረንሳይ ግብጽን፣ ሰፔን ደግሞ ሞሮኮን አሸንፈው ነው ለዚህ የደረሱት። በቴሪ ሆንሪ የምትመራው ፈረንሳይ በውድድሩ በተጠበቀችው ልክ ጠንካራ ኾና ዘልቃለች።

ስፔኖችም ዋናው ብሔራዊ ቡድን በሚታወቅበት ኳስን የመቆጣጠር አጨዋወት ስልት ታግዘው ለዛሬው ፍጻሜ ደርሰዋል።

ለነሀስ ሜዳልያ ትናንት በተደረገ ጨዋታ ሞሮኮ ግብጽን 6 ለ 0 በማሸነፍ ሦስተኛ መኾኗን አረጋግጧለች።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here