ባሕር ዳር: ነሐሴ 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የ5000 ሜትር ወንዶች ማጣሪያ የተወዳደሩት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ፍፃሜ አልፈዋል ።
አትሌት ሐጎስ ገብረሕይወት ከምድብ አንድ በ 14:08:18 ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ
አትሌት ቢኒያም መሐሪ ከምድብ ሁለት 13:51:82 በሁለተኛ ደረጃ በማጠናቀቅ እንዲሁም
አትሌት አዲሱ ይሁኔ ከምድብ ሁለት 13:52:62 ስምንተኛ ደረጃ በመያዝ ወደ ፍጻሜ ማለፍ ችሏል ።
የፍጻሜው ውድድር ነሐሴ 4/ 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2:50 ላይ ይካሄዳል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!