ባሕር ዳር: ሐምሌ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የማንቸስተር ሲቲው ጁሊያን አልቫሬዝ አትሌቲኮ ማድሪድን ለመቀላቀል ጫፍ ደርሷል። ሁለቱ ክለቦች በዝውውር ሂሳቡ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ቢቢሲ በስፖርት ገጹ አስነብቧል። ፖርቱጋላዊ ጆኦ ፍሊክስ የዝውውሩ አካል በመኾን በውሰት ወደ ሲቲ ሊያመራ ይችላልም ተብሏል።
የስፔኑ ክለብ ከአልቫሬዝ በተጨማሪ ኮነር ጋላገርን ከቼልሲ ለማስፈረም መስማማቱም ተገልጿል።
በቴሌግራፍ ዘገባ መሰረት ደግሞ አንግሊዛዊ ተከላካይ ማርክ ጉሂ ኒውካስትልን ለመቀላቀል ጫፍ ደርሷል። የክርስቲያል ፓላሱ ተከላካይ ማንቸስተር ዩናይትድን ጨምሮ በብዙ ታላላቅ ክለቦች ሲፈልግ ነበር።
ማንቸስተር ዩናይትድ ማኑኤል ኡጋርቴን ከፒኤስጅ ለመስፈረም የነበረው ፍላጎት መቀዛቀዙን የዘገበው ደግሞ ዘ አትሌቲክ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!