ባሕር ዳር: ሐምሌ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ ምሽት 3፡50 ላይ በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር የፍጻሜ ውድድር ቢኖርም ኢትዮጵያውያኑ አብዲሳ ፈይሳ በመጀመሪያው ዙር ማጣሪያ፣ ኤርሚያስ ግርማና ሳሙኤል ተፈራ ደግሞ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ከውድድሩ በመሰናበታቸው ኢትዮጵያን ወክሎ በፍጻሜው የሚሳተፍ አትሌት የለም፡፡
ይሁን እንጂ ምሽት 4፡10 ላይ በሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል የፍጻሜ ውድድር ሲካሄድ ኢትዮጵያውያኑ ሲምቦ አለማየሁ እና ሎሚ ሙለታ ለሜዳልያ ተፋላሚዎች ናቸው፡፡
መልካም ውጤት ለኢትዮጵያውያንⵑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!