ተጠባቂው የ5 ሺህ እና 800ሜትር ሴቶች ፍጻሜ ዛሬ ማምሻውን ይካሄዳል።

0
187

ባሕር ዳር: ሐምሌ 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በ5000ሜትር እና 800ሜትር ሴቶች የሚደረገውን የፍጻሜ ውድድር በጉጉት የሚጠበቅ ነው።

5000 ሜትር የሴቶች ፍፃሜ ውድድር
👉አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ
👉አትሌት እጅጋየሁ ታዬ
👉አትሌት መዲና ኢሳ ኢትዮጵያን ይወክላሉ።
👉ውድድሩ ከምሽቱ 4:15 ላይ ይካሄዳል ።
👉ፍጻሜው በ ስታድ ደ ፍራንስ ብሔራዊ ስቴድየም ይከናወናል። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚያደርጉት ፍልሚያ በስፖርት ቤተሰቡ በጉጉት ይጠበቃል።

የ 800ሜትር የሴቶች ፍጻሜ ውድድር ተሳታፊዎች
👉አትሌት ፅጌ ዱጉማ እና
👉 አትሌት ወርቅነሽ መለሰ ኢትዮጵያን በመወከል ከምሽቱ 4:47 ይወዳደራሉ ።
👉የግማሽ ፍጻሜ ውድድራቸውን አትሌት ፅጌ ከምድብዋ አንደኛ እንዲሁም ወርቅነሽ መለሰ 2ኛ በመውጣት ለፍጻሜ ማለፋቸውን የሚታወስ ነው።
ሌላው ውድድር ደግሞ የ3000ሜትር ወንዶች መሰናክል ማጣሪያ ውድድር ዛሬ ማታ 2:04 ይካሄዳል።

👉 አትሌት ለሜቻ ግርማ
👉 አትሌትጌትነት ዋለና
👉አትሌት ሳሙኤል ፍሬው ይሳተፋሉ።
👉የፍጻሜው ውድድር ነሐሴ 1/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 4:43 እንደሚካሄድ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መልካም እድል ለአትሌቶቻችን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here