ባሕር ዳር: ሐምሌ 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዓለም አቀፉ የጄ ኬ ኤስ ካራቴ ሻምፒዮና ተወዳድረው ለኢትዮጵያ ሜዳልያ ላመጡት ኢንስትራክተር አብርሃም ንጋቱ፣ ኢንስትራክተር ነቢል ካሳሁን እና ሰንሴ ኤፍሬም አደም በኮምቦልቻ ከተማ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በውድድሩ ኢንስትራክተር ነቢል ካሳሁን ለሃገሩ ነሀስ ያመጣ ሲኾን ኢንስትራክተር አብርሀም ንጋቱ እና ሰንሴ ኤፍሬም አደም ደግሞ አራተኛ በመውጣት ዲፕሎማ ማምጣታቸው ይታወሳል።
ከኮምቦልቻ እና ወልድያ ከተማ የተገኙት ተወዳዳሪዎቹ በዛሬው እለት ኮምቦልቻ ከተማ ሲገቡ በከተማዋ የስፖርት ቤተሰቦች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈችበት በዚህ ሻምፒዮና ሁለት የነሃስ ሜዳሊያ እና በሁለት ስፖርተኞች ዲፕሎማ መገኘቱ ተገልጿል።
ዘጋቢ:- ተመስገን አሰፋ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!