ኢትዮጵያውያን የሚሳተፉባቸው የዛሬ የኦሎምፒክ መርሐ-ግብሮች

0
308

ባሕር ዳር: ሐምሌ 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የ2024ቱ ኦሎምፒክ ዛሬም በበርካታ ውድድሮች ይቀጥላል። ዛሬ ከሚካሄዱ ውድድሮች መካከል ኢትዮጵያውያን የሚሳተፍባቸው ውድድሮች ይገኙበታል።

በጉጉት የሚጠበቀው የወንዶች 10 ሺህ ሜትር የሚከናወነው ዛሬ ነው። የአትሌቲክስ ውድድሮች ዘግይተው በመጀመራቸው እስካሁን ሜዳሊያ ውስጥ ያልገባችው ኢትዮጵያ ዛሬ ሜዳልያ እንደምታስመዘግብ ይጠበቃል። ሰለሞን ባረጋ፣ በሪሁ አረጋዊ እና ዮሚፍ ቀጀልቻ አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀዩን ሰንደቅ ከፍ ለማድረግ ምሽት 4:20 ይወዳደራሉ። ሰለሞን ከአራት ዓመት በፊት በኦሎምፒክ አሸንፎ ሀገሩን ማኩራቱም ይታወሳል። የዛሬውን ውድድር ለማሸነፍም ትልቅ ግምት አግኝቷል።

በሪሁ እና ዮሚፍም በርቀቱ ልምድ እና ጥሩ ሰዓት ያላቸው በመኾኑ በተመሳሳይ ጥሩ ውጤት እንደሚያስመዝግቡ ግምት አግኝተዋል። ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ የኡጋንዳ እና የኬንያ አትሌቶችም 10 ሺህ ሜትሩን ለማሸነፍ ግምት ካገኙት ውስጥ እንደሚገኙ ወርልድ አትሌቲክስ አስነብቧል።

የወንዶች የ10 ሺህ ሜትር የኦሎምፒክ ክበረወሰን በቀነኒሳ በቀለ እጅ ይገኛል። አትሌቱ በቤጅንግ ኦሎምፒክ ርቀቱን ያሸነፈበት 27 ደቂቃ 01 ሴኮንድ ከ17 ማይክሮ ሴኮንድ ነው በክበረወሰንነት የተመዘገበው።

ከ10 ሺህ ሜትር በፊት ኢትዮጵያውያን በማጣሪያ ውድድር በተለያዩ ርቀቶች ይወዳደራሉ። የወንዶች 1500 የማጣሪያ ውድድር ቀን 6:10 ጀምሮ ይካሄዳል። አብዲሳ ፈይሳ፣ ኤርሚያስ ግርማ እና ሳሙኤል ተፈራ ደግሞ በርቀቱ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ናቸው።

ሌላኛው የዛሬ የኢትዮጵያውያን መርሐ-ግብር የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ ነው። መዲና ኢሳ፣ እጅጋየሁ ታየ እና ተጠበቂዋ ጉዳፍ ፀጋየ ደግሞ በርቀቱ ሀገራቸውን ወክለዋል። ውድድሩ ምሽት 1:10 ጀምሮ ይካሄዳል።

ምሽት 2:45 ጀምሮ ደግሞ ሀብታም አለሙ፣ ጽጌ ደጉማ እና ወርቅነሽ መሰለ የሚካፈሉበት የ800 ሜትር የሴቶች ማጣሪያ ይከናወናል።

ድል ለኢትዮጵያውያን አትሌቶች!

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here