የሻምበል አበበ ቢቂላ ውርስ በፓሪስ

0
284

ባሕር ዳር: ሐምሌ 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በፓሪስ ኦሎምፒክ ሻምበል አበበ ቢቂላን ለማስታወስ በባዶ እግሩ ለሚሮጠው ኤርሚያስ ይርጋ ሽኝት ተደረገለት።

የባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር የሻምበል አበበ ቢቂላን ፈለግ በመከተል በኦሎምፒክ መድረክ በባዶ እግሩ ለሚሮጠው ኤርሚያስ ይርጋ ሽኝት አድርጎለታል፡፡

የባሕል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በሽኝት መርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው በ1960 የሮም ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ አደባባይ መድረክ ስሟ ከፍ ብሎ እንዲጠራ ካደረጉ የኦሎምፒክ ጀግኖች መካከል ቀዳሚው አበበ ቢቂላ መኾኑን አንስተዋል፡፡

ሚኒስትሯ የሻምበል አበበ ቢቂላን አርዓያነት በመከተል በባዶ እግር በመሮጥ የሀገርን ስም ለማስጠራት እና አትሌቱን ለማስታወስ በሚያካሂደው ሩጫ ድል እንዲቀናው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

የስፖርት ዘረፍ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት በዓለም አደባባይ በባዶ እግር በመሮጥ ኦሎምፒክን ያሸነፈውን ብቸኛው አፍሪካዊ አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላን ገድል መዘከር የሁሉም ትውልድ ኀላፊነት እንደኾነ አብራርተዋል፡፡

በትውልድ ቅብብሎሽ ዛሬም በባዶ እግር መሮጥ እንደሚቻል እና የቀደምት ጀግና ታሪክን ይዞ ለማስቀጠል ወደ ፓሪስ በማቅናት በባዶ እግሩ ለሚሮጠው ኤርሚያስ ይርጋ ክብር ይገባዋል ብለዋል፡፡

የቀድሞ ሞተር ስፖርት ማኅበር ፕሬዚዳንት እና የቀድሞ የኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫ ዋና ሥራ አሥኪያጅ ኤሪሚያስ ይርጋ በሮም፣ በአቴንስ፣ በደቡብ ኮሪያ እና በእንግሊዝ በተካሄዱ ኦሎምፒኮች ላይ በባዶ እግራቸው በመሮጥ ሻምበል አበበ ቢቂላን ማስታወስ እንደቻሉ መግለጻቸውን ከባሕል ስፖርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here