በፓሪስ ኦሎምፒክ ለመሳተፍ ላቀናው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ደማቅ አቀባበል ተደረገለት።

0
206

ባሕር ዳር: ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በፈረንሳይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በፓሪስ ኦሎምፒክ ለመሳተፍ ወደ ስፍራው ላቀናው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

አቀባበሉ የተደረገው በነገው ዕለት ዓርብ ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በይፋ በሚጀመረው 33ኛው የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክና ፓራሊምፒክ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን በመወከል ለሚሳተፈውና በመጀመሪያው ዙር ፓሪስ ለገባው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ነው።

በወቅቱም ፓሪስ የሚገኘው የኢፌዴሪ ሚሲዮን በፈረንሳይ ከሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት ጋር በመኾን ቻርልስ ደጎል ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝቶ ለኦሎምፒክ ቡድኑ ልዩ አቀባበል አድርጓል።

ዝግጅቱ ሀገራችንን ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር እንደሆነም ከሚሲዮኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here