ዛሬ የተሰሙ የዝውውር ወሬዎች

0
406

ባሕርዳር: ታኅሳሥ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሪያል ማድሪድ የኤቨርተኑን የመሐል ተከላካይ ጃራርድ ብራንትዋይትን ለማስፈረም ድርድር ላይ ይገኛል ሲል ሜል ዘግቧል፡፡
የ22 ዓመቱ ቤልጄማዊው አማካይ አማዱ ኦናና ወደ አርሰናል የመዛወር ፍላጎት አለው ሲል ቢቢሲ አስነብቧል፡፡ ማንቸስተር ዩናይትድም ከኦናና ጋር ንግግር መጀመሩን ዘገባው አስታውሷል፡፡

አስቶንቪላ የ23 ዓመቱን ካናዳዊ የፊት መስመር ተጫዋች ጆናታን ዴቪድን ከፈረንሳዩ ሊል ቡድን ለማስፈረም ፍላጎቱን አሳይቷል ሲል ሜል ዘግቧል፡፡ የ21 ዓመቱ የሊቨርፑል አማካኝ ፋቢዮ ካርቫልኾ በውድድር ዓመቱ በውሰት የእንግሊዙን ሃል ሲቲ ቡድን ሊቀላቀል ነው።

የሳዑዲ አረቢያው ቡድን አል ኢቲፋቅ እንግሊዛዊ አማካኝ ጆርዳን ሄንደርሰንን በዚህ ወር የዝውውር ጊዜ ማጣት አልፈልግም ማለቱን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡ባየር ሙኒክ እና ባየር ሊቨርኩሰን የሄንደርሰን ፈላጊዎች ናቸው ሲል ቶክስፖርት በድረ ገጹ አስነብቧል ፡፡

እንግሊዛዊ አማካይ ካልቪን ፊሊፕስን ለማስፈረም ማንቸስተር ሲቲ እና ኒውካስትል ንግግር መጀመራቸውን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡ ዎልቭስ የፓሪስ ሴንት ዠርሜን ፈረንሳዊ የፊት መስመር አጥቂ ሁጎ ኤክኪኬን ማስፈረም ይፈልጋሉ ተብሏል፡፡

ፒኤስቪ አይንድሆቨን እና ኤልኤ ጋላክሲ የ22 ዓመቱን ዑራጓዊ አጥቂ ፋኩንዶ ፔሊስትሪን ከማንቸስተር ዩናይትድ ለማስፈረም ፍላጎት ማሳየታቸውን ዴይሊ ሜይልን ጠቅሶ ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ኢያን ማሴን በውሰት ውል ከቼልሲ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ ብራይተን የ19 ዓመቱን አርጀንቲናዊ የግራ መስመር ተከላካይ ቫለንቲን ባርኮን ከቦካ ጁኒየርስ ለማስፈረም 10ሚሊዮን ዩሮ የውል ማፍረሻ ሊያቀርብ ነው። ኤሲሚላን የ23 ዓመቱን ቤልጂየማዊ የፊት መስመር አጥቂ ሲሪል ንጎንጌ ለማስፈረም ፍላጎታቸውን አሳይተዋል ሲል ቢቢሲ ስፖርት በድረ ገጹ አስነብቧል፡፡

በሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here