በኮምቦልቻ ከተማ የበጋ ወራት የስፖርት ውድድሮች ማጠቃለያ መርሐግብር ተካሄደ።

0
258

ባሕር ዳር: ሰኔ 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ወጣት እና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አስቻለው ብርሀኑ ከመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት መምሪያው አጠቃላይ በበጋ ወራት ሲያካሂዳቸው የቆዩ ስፖርቶችን የመዝጊያ መርሐግብር አካሂዷል።

በበጋ ወራት እንደ ከተማ 56 ቡድኖች መሳተፋቸውን ገልጸዋል። 56 ቡድኖች በ5 ምድብ ውድድር ሲያካሂዱ ቆይተዋል ያሉት መምሪያ ኃላፊው በህጻናት፣ በልዩ ህጻናት፣ በወጣት እና በጤና ቡድን ውድድሮች ሲካሄዱ መቆየታቸውን አብራርተዋል። አያይዘውም ጨዋታውን በባለሙያዎች ለመዳኘት ከፌደራል ዳኞችን በማስመጣት 10 ዳኞችን አብቅቶ ፈቃድ በማሰጠት ጨዋታውን ብቃት ባላቸው ዳኞች ማጫዎት መቻሉን አቶ አስቻለው ብርሀኑ ጨምረው ገልጸዋል።

የበጋ ወራት አጠቃላይ ስፖርት ተሳታፊ ቡድኖች የዋንጫ፣ የትጥቅ፣ የሰርተፊኬት እውቅና እና ሽልማት ተሰጥቷል ብለዋል። በበጋ ወራት የነበረውን ስፖርታዊ መነቃቃት በክፍለ ከተሞች በክረምቱም ለማስቀጠል መምሪያው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደረግ መናገራቸውን የኮምቦልቻ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያሳያል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here