ፋሲል ከነማ እና ባሕር ዳር ከተማ የዓመቱ ጉዟቸውን ዛሬ ያጠናቅቃሉ።

0
181

ባሕር ዳር: ሰኔ 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ30ኛ ሳምንት የዛሬ መርሐ ግብር ቀን 9 ሰዓት ቅዱስ ጊዮርጊስን ከፋሲል ከነማ አገናኝቷል። ጨዋታው በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተደረገ ነው። በቅርቡ ዋና አሠልጣኙን ያሰናበቱት ፈረሰኞቹ 29 ጨዋታዎችን አድርገው በስምንት ጨዋታዎች ተሸንፈው በዘጠኝ ጨዋታዎች አቻ ተለያይተው በ12 ጨዋታዎች በማሸነፍ 45 ነጥብ በአምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

የጊዮርጊስ ተጋጣሚ ፋሲል ከነማ በአጥቂ እና በተከላካይ መስመር ጠንካራ ተጫዋቾችን ቢያሰባስብም ደረጃው የሚያኩራራ አይደለም። ቡድኑ ካደረጋቸው 29 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በ11 ጨዋታዎች ብቻ ነው።በሰባት ጨዋታዎች ተሸንፎ እና በ11 ጨዋታዎች አቻ ተለያይቶ በ44 ነጥብ በስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

አጼዎቹ የዛሬው ጨዋታ ማሸነፍ ከቻሉ ነጥባቸውን 47 በማድረስ ደረጃቸውን በአንድ አሻሽለው ዓመቱን ያጠናቅቃሉ። ምሽት 12ሰዓት ደግሞ ሲዳማ ቡና ከባሕር ዳር ከተማ ይጫወታሉ። የጣና ሞገዱ ከደረጋቸው 29 ጨዋታዎች በ13 አሸንፎ፣በ11 አቻ ተለያይቶ እና በአምስት ጨዋታዎች ተሸንፎ ነጥቡን 50 በማድረስ በአራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ቡድኑ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ የውድድር ዓመቱን በሦስተኛ ደረጃን በመያዝ በክብር የሚያጠናቅቅ ይኾናል።

ተጋጣሚው ሲዳማ ቡና ባሕር ዳር ከተማን ካሸነፈ ደግሞ አሁን ካለበት 12ኛ ደረጃ ሁለት ደረጃዎችን በማሻሻል 10 ኛን በመያዝ የዓመቱን ውድድር ይጨርሳል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here