ማንቸስተር ዩናይትድ የኤሪክ ቴንሀግን ውል አራዘመ።

0
177

ባሕር ዳር: ሰኔ 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ማንቸስተር ዩናይትድ አሠልጣኝ ቴንሀግን ለቀጣይ ሁለት ዓመታት በክለቡ እንዲቆዩ ውላቸውን አራዝሟል። ክለቡ አዲስ አሠልጣኝ ለመቅጠር ፍላጎት አለው ሲባል ከቆየ በኋላ ኔዘርላንዳዊን አሠልጣኝ ለማቆየት ወስኗል። ቴንሀግ በማንቸስተር ዩናይትድ በቀጣይነት ለመሥራት ውላቸውን በማረዘማቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ባለፍት ሁለት ዓመታት ሁለት ዋንጫ ማሳካታቸውን በማንሳት ክለቡ መሻሻል ላይ መኾኑን አንስተዋል። ነገር ግን የሚቀሩ ጠንካራ ሥራዎች አሉ ብለዋል። ከክለቡ ጋር በቀጣይ ግቦች ዙሪያ ተነጋግረናል፣ ተግባብተናልም ማለታቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here